መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 85

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ ለምድርህ ሞገስ አሳየህ የያዕቆብን ምርኮ መለስህ፡፡
2የሕዝብህን ኃጢአት ይቅር አልህ በደላቸውንም ሸፈንህ፡፡ ሴላ
3መዓትህን ሁሉ አራቅህ ከጽኑ ቁጣህም ተመለስህ፡፡
4አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ፣ መልሰን፤ በእኛ ያዘንህብንን ሁሉ አርቅልን፡፡
5የምትቆጣን ለዘላለም ነውን? ቁጣህንስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ታስተላልፋለህን?
6እኛ ሕዝብህ በአንተ ደስ እንዲለን እንደ ገና በሕይወት አታኖረንምን?
7ያህዌ ሆይ፣ የኪዳን ታማኝነትህን አሳየን ማዳንህንም ስጠን፡፡
8ያህዌ አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ እንደ ገና በስሕተት መንገድ ካልሄዱ በቀር ለሕዝቡና ለታማኞቹ ሰላምን ያደርጋል፡፡
9ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ ማዳኑ ለሚፈሩት በእርግጥ ቅርብ ነው፡፡
10ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፡ ጽድቅና ሰላም ተሳሳሙ፡፡
11ታማኝነት ከምድር በቀለች ጽድቅ ከሰማይ ተመለከተች፡፡
12ያህዌ መልካም ነገር ይሰጣል ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች፡፡
13ጽድቅ በፊቱ ትሄዳለች ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።