መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 84

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ ማደሪያህ ምንኛ ያማረ ነው፡፡
2ነፍሴ የያህዌን አደባባዮች ትናፍቃለች እጅግም ትጓጓለች፡፡ ልቤና ሁለንተናዬ ሕያው እግዚአብሔርን ይጣራሉ፡፡
3ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ መሠዊያህ ባለበት ስፍራ ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቦታ አገኘች፡፡
4በቤትህ የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱ ለዘላለም ያመሰግኑሃል፡፡ ሴላ
5አንተን ብርታታቸው ያደረጉ በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ ቡሩካን ናቸው፡፡
6በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ የሚጠጡት የምንጭ ውሃ ያገኛሉ የበልግም ዝናብ ይሞላዋል፡፡
7ከኃይል ወደ ኃይል ይሸጋገራሉ እያንዳንዱም በጽዮን ባለው አምላክ ፊት ይቀርባል፡፡
8የሰራዊት አምላክ ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፣ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ቃሌን አድምጥ፡፡ ሴላ
9አምላክ ሆይ፣ ጋሻችንን ጠብቅ፣ ለቀባኸውም ራራለት፡፡
10በሌላ ቦታ ሺህ ቀን ከመኖር፣ አንዲት ቀን በአደባባይህ መዋል ይሻላል፡፡
11አምላካችን ያህዌ ፀሐይና ጋሻችን ነውና፤ ያህዌ ጸጋንና ክብርን ይሰጣል፤ በቅንነት የሚሄዱትን መልካም ነገር አይነፍጋቸውም፡፡
12የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በአንተ የተማመነ ሰው ቡሩክ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።