መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 83

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሆይ፣ ዝም አትበል አትተወን ችላ አትበል፡፡
2ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት፡፡
3በሕዝብህ ላይ ያደባሉ፣ አንተ በምትጠብቃቸውም ላይ ያሣራሉ፡፡
4‹የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታሰብ፣ ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው» አሉ፡፡
5በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ አንተም ላይ ተማማሉ፡፡
6የኤዶምና የእስማኤላውያን፣ የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣
7ጌባል አሞንና አማሌቅ፣ ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር አብረው ዶለቱ፡፡
8አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ የሎጥም ልጆች ረዳት ሆነ፡፡ ሴላ
9ምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው በቂሶን ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው፡፡
10እነርሱ በዐይንዶር ጠፉ እንደ ምድር ትቢያ ሆኑ፡፡
11እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣ መሳፍንቶቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤
12እነርሱም፣ «የእግዚአብሔርን ግጦሽ ቦታ እንውሰድ» አሉ፡፡
13አምላኬ ሆይ፣ በዐውሎ ነፋስ እንደሚወሰድ ትቢያ፣ ነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው፡፡
14እሳት ደንን እንደሚያቃጥል ተራራውን እንደሚያዳርስ እሳት ነበልባል
15እንዲሁ በማዕበልህ አሳዳቸው በሞገድህም አስደንግጣቸው፡፡
16አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ ፊታቸውን በእፍረት ሙላ፤
17ለዘላለም ይፈሩ ይታወኩም፤ በውርደትም ይጥፉ፡፡
18ስምህ ያህዌ የሆነው አንተ ብቻ በምድር ላይ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።