መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 82

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ ቆመ፤ በአማልክትም ላይ፣ ይፈርዳል እንዲህም ይላል፤
2ፍትሕ የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው? ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው? ሴላ
3ለድኾችና ለሙት ልጆች ተሟገቱ፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ፡፡
4ድኾችንና ምስኪኖችን ታደጉ፤ ከዐመፀኞችም እጅ አስጥሏቸው፡፡
5ዕውቀትም ሆነ ማስተዋል የላቸውም በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ የምድር መሠረቶችም ተናወጡ፡፡
6እኔም፣ «እናንተ አማልክት ናችሁ፤ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ አልሁ፡፡
7ሆኖም፣ እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ፡፡»
8እግዚአብሔር ሆይ፣ ተነሥ፤ ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና፤ በምድር ላይ ፍረድ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።