መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 81

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ብርታታችን ለሆነው አምላክ በደስታ ዘምሩ ለያዕቆብ አምላክ በደስታ እልል በሉ፡፡
2ለመዘመር ተነሡ፤ ከበሮም ምቱ በበገናና በመሰንቆ ደስ የሚል ዜማ አሰሙ፡፡
3በሙሉ ጨረቃ በክብረ በዓላችን ቀን በወሩ መግቢያ ጨረቃ ስትወለድ ቀንደ መለከት ንፉ፡፡
4ይህም ለእስራኤል የተደነገገ፣ የያዕቆብ አምላክ የሰጠው ሥርዐት ነው፡፡
5ግብፅን ለቅቆ በወጣ ጊዜ ይህን ለዮሴፍ ደነገገ፤ በማላውቀውም ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤
6«ከትከሻው ሸክምን አስወገድሁ እጆቹንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ፡፡
7በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ረዳሁህ በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ፡፡ ሴላ
8ሕዝቤ ሆይ፣ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ እስራኤል ሆይ፣ ምነው ባደመጥኸኝ!
9ባዕድ አምላክ በመካከልህ አይሁን ሌሎች አማልክት አታምልክ፡፡
10እኔ ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ ያህዌ ነኝ፡፡ አፍህን በሰፊው ክፈት፤ እኔም እሞላዋለሁ፡፡
11ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰማም እስራኤልም ለእኔ አልታዘዝም፡፡
12ስለዚህ በእልከኝነት መንገዳቸው እንዲሄዱ፣ የፈለጉትንም እንዲያደርጉ ተውኳቸው፡፡
13ምነው ሕዝቤ ባደመጠኝ ኖሮ፣ እስራኤል በመንገዴ ሄዶ ቢሆን ኖሮ፡፡
14ፈጥኜ ጠላቶቻቸውን አስገዛላቸው ነበር እጄንም በጨቋኞቻቸው ላይ ባነሣሁ ነበር፡፡
15ያህዌን የሚጠሉ በፊቱ በፍርሃት ይሸማቀቃሉ! ለዘላለምም ያፍራሉ፡፡
16እስራኤልን ግን ምርጡን ስንዴ አበላዋለሁ ከዐለት ከሚገኘውም ማር አጠግባችኋለሁ፡፡»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።