1ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፣ ስማን፡፡ በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፣ ብርሃንህ ይብራልን!
2በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ኃይልህን ግለጥ፤ መጥተህም አድነን፡፡
3አምላክ ሆይ፣ መልሰን ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡
4የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በሕዝብህ ጸሎት ላይ የምትቆጣው እስከ መቼ ነው?
5የእንባ እንጀራ አበላሃቸው ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው፡፡
6የጐረቤቶቻችን መከራከሪያ አደረግኸን ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን፡፡
7የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡
8የወይን ግንድ ከግብፅ አመጣህ አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልህ፡፡
9መሬቱን መነጠርህላት፣ እርሷም ሥር ሰድዳ መሬቱን ሞላች፡፡
10ተራሮችም በጥላዋ ተሸፈኑ የቅርንጫፎቿም ጥላ የሊባኖስን ዛፎች ሸፈነ፡፡
11ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ ቁጥቋጦዋንም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ዘረጋች፡፡
12ታዲያ፣ አላፊ፣ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲቀጥፍ በዙሪያዋ የነበሩ አጥሮችን ለምን አፈረስህ፡፡
13የዱር አሳማ ያበላሻታል በሜዳ የሚንጋጋም አራዊት ይበላታል፡፡
14የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ ወደ እኛ ተመለስ፣ ከሰማይ ተመልከት እይም ይህችን የወይን ተክልም ተንከባከባት፡፡
15ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ተክል አንተም ያጸደቅሃት ተክል ናት፡፡
16ነገር ግን ቆራርጠው በእሳት አቃጠሏት ከቁጣህ የተነሣ ይጠፋሉ፡፡
17እጅህ የቀኝ እጅህ የሆነው ሰው ላይ፣ አንተ ራስህ ብርቱ ያደረግኸው የሰው ልጅ ላይ ትሁን
18እኛም ከአንተ ወደ ኋላ አንልም፤ በሕይወት ጠብቀን፤ እኛም ስምህን እንጠራለን፡፡
19ሰራዊት አምላክ ያህዌ ሆይ፣ መልሰን ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡