1አምላክ ሆይ፣ ባዕድ ሕዝቦች ርስትህን ወረሩ! የተቀደሰ መቅደስህን አረከሱ ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አደረጓት፡፡
2የባሪያዎችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣ የታማኞችህን ሥጋ ለምድር አራዊት ምግብ እንዲሆን ሰጡ፡፡
3ደማቸውን በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ የሚቀብራቸውም አልተገኘም፡፡
4እኛም ለጐረቤቶቻችን መዘባበቻ በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን፡፡
5ያህዌ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ነው? የምትቆጣው ለዘላለም ነውን? ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?
6አንተን በማያውቁ ሕዝቦች ላይ፣ ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ መዓትህን አፍስስ፤
7ያዕቆብን ውጠውታልና መኖሪያ ቦታውንም ባድማ አድርገዋል፡፡
8የአባቶቻችንን ኃጢአት እኛ ላይ አትቁጠርብን እጅግ ተዋርደናልና ምሕረትህ ፈጥና ወደ እኛ ትምጣ፡፡
9መድኃኒታችን እግዚአብሔር ሆይ፣ ስለ ስምህ ክብር ርዳን፤ ይቅርም በለን፡፡
10ሕዝቦች፣ «አምካቸው የት አለ?» ለምን ይበሉ? ስለ ፈሰሰው የባሪያዎችህ ደም፣ ዐይናችን እያየ ሕዝቦችን ተበቀል፡፡
11የእስረኞች ሰቆቃ ወደ አንተ ይድረስ በኃይልህ ብርታት ሞት የተፈረደባቸውን አድን፡፡
12ጌታ ሆይ፣ ጐረቤቶቻችን አንተ ላይ ስለ ሰነዘሩት ስድብ ሰባት ዕጥፍ ተበቀላቸው፡፡
13እኛ ሕዝብህ፣ የመሰማሪያ በጐችህ ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፡፡ ለትውልድ ሁሉ ምስጋናህን እንናገራለን፡፡