1ክብርህን በላይ በሰማያት የምትገልጥ አንተ ጌታችን ያህዌ፣ ስምህ በምድር ሁሉ ምንኛ ገናና ነው፡፡
2ከጠላትህ የተነሣ፤ ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ለማሰኘት ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡
3ጣቶችህ የሠሯቸው ሰማያትን፣ በየቦታቸው ያደርግሃቸው ጨረቃና ከዋክብትን ስመለከት
4በአሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጠነቀቅለትስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
5ከመላእከት በጥቂት አሳነሰኸው የክብርና የሞገስ ዘውድ አቀዳጀኸው፡፡
6በእጆችህ ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አደረግህለት
7በጐችና በሬዎችን፣ የዱር አራዊትን፣
8የሰማይ ወፎችን፣ የባሕር ዓሦችን ባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትን ሁሉ አስገዛህለት፡፡
9ጌታችን ያህዌ፣ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ገነነ!