መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 76

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው፡፡
2ድንኳኑ በሳሌም መኖሪያውም በጽዮን ነው፡፡
3በዚያም የቀስቱን ፍላጻዎች ጋሻውን፣ ጦሩንና ሌሎች የጦር መሣሪያዎችን ሰበረ፡፡ ሴላ
4ጠላቶችህን ካጠፋህበት ተራሮች ስትወርድ ደምቀህ አበራህ፤ ክብርህንም ገለጥህ፡፡
5ጀግኖች ተኝተው እያሉ የማረኩትን ተቀሙ ጦረኞችም ሁሉ ዐቅመ ቢስ ሆኑ፡፡
6የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሱና ፈረሰኛው ጭልጥ ብለው ተኝተዋል፡፡
7መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤ በተቆጣህ ጊዜ ፊትህ መቆም የሚችል ማነው?
8አንተ ከሰማይ ፍርድህን አሰማህ ምድርም ፈርታ ጸጥ አለች
9አንተ በምድር የተጨቆኑትን ለማዳን ለፍርድ ስትነሣ ዓለም ጸጥ አለ፡፡
10በእርግጥ የሰው ልጅ ላይ የሚወርደው ቁጣ ፍርድህ አንተን ያመሰግንሃል ከቁጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ፡፡
11ለአምላካችሁ ለያህዌ ተሳሉ፣ ስእለቱንም አግቡ በእርሱ ዙሪያ ያሉ ሁሉ መፈራት ለሚገባው እጅ መንሻ ያምጡ፡፡
12እርሱ የገዦችን መንፈስ ይሰብራል በምድር ነገሥታትም ዘንድ የተፈራ ይሆናል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።