መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 75

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አምላክ ሆይ፣ እናመሰግንሃለን ሐልዎትህን ስለ ገለጥህ ምስጋና ለአንተ እንሰጣለን፤ ሰዎች ድንቅ ሥራህን ይናገራሉ፡፡
2አንተም እንዲህ አልህ፣ «ለይቼ በወሰንሁት ሰዓት በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ፡፡
3ምድር ብትናወጥ በውስጧ የሚኖሩትም ቢንቀጠቀጡ እኔ የምድርን መሠረት አጸናለሁ፡፡ ሴላ፡፡
4ትዕቢተኞችን፣ አትታበዩ ክፉዎችን ‹አታምፁ› እላቸዋለሁ፤
5ቀንድህን ወደ ሰማይ አታንሣ፤ ዐንገትህንም መዝዘህ አትናገር፡፡»
6ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣም፡፡
7ነገር ግን አንዱን ዝቅ፣ ሌላውን ከፍ በማድረግ በትክክል የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፡፡
8ያህዌ በእጁ የቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ ይዞአል ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ጨልጠው ይጠጡታል፡፡
9እኔ ግን ዘወትር ሥራህን እናገራለሁ፤ ለያዕቆብ አምላክም ዝማሬ አቀርባለሁ፡፡
10እርሱ «የክፉዎችን ሁሉ ቀንድ እሰብራለሁ፤ የጻድቃን ቀንድ ግን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ» ይላል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።