1አምላክ ሆይ አድነኝ፤ ያህዌ ሆይ፣ ፈጥነህም እርዳኝ፡፡
2ሕይወቴን ማጥፋት የሚፈልጉ ይፈሩ ይዋረዱም፤
3በእኔ ስቃይ ደስ የሚላቸው ተሸማቅቀው ወደ ኋላ ይመለሱ፡፡
4ነገር ግን አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፤ ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ሁልጊዜ፣ «እግዚአብሔር ታላቅ ነው» ይበሉ፡፡
5እኔ ምስኪንና ችግረኛ ነኝ፤ አምላክ ሆይ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ አንተ ረዳቴ ታዳጊዬም ነህና ያህዌ ሆይ አትዘግይ፡፡