መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 68

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ይነሣ የሚጠሉትም ከፊቱ ይበተኑ፡፡
2ጢስ እንደሚበንን፣ እንዲሁ አብንናቸው፤ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ እንዲሁ ክፉች ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ፡፡
3ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ ደስታንና ሐሤትን ይሞሉ፡፡
4ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም የምስጋና መዝሙር አቅርቡ በደመናት ላይ የሚሄደውን ከፍ አድርጉት፡፡ ስሙ ያህዌ ነው! በፊቱም ሐሤት አድርጉ፡፡
5በተቀደሰ ማደሪያው ያለው አምላክ አባት ለሌላቸው አባት ነው፡፡ ለመበለቶችም ዳኛ ነው፡፡
6እግዚአብሔር ብቸኞች በቤተ ሰብ መካከል ያኖራቸዋል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃቸዋል፤ ክፉዎች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ፡፡
7እግዚአብሔር ሆይ፣ በሕዝብህ ፊት ባለፍህ ጊዜ በምድረ በዳ በተጓዝህ ጊዜ፣
8በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ምድር ተንቀጠቀጠች ሰማያትም ዶፍ አወረዱ፡፡
9እግዚአብሔር ሆይ፣ በቂ ዝናብ አዘነብህ ደርቆ የነበረውን ርስትህን አረሰረስህ፡፡
10ሕዝብህ መኖሪያው አደረጋት፤ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ከመልካምነትህ ለድኾች ሰጠህ፡፡
11እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ቃሉን ሰጠ ቃሉን የሚያውጁትም ብዙ ሰራዊት ናቸው፡፡
12-13የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ወደ ኋላ ሸሹ፤ በሰፈር የቀሩ ሴቶችም ምርኮ ተከፋፈሉ በበጐች በረት መካከል ብትገኙ እንኳ በቅጠልያ ወርቅ እንደ ተለበጡ ላባዎች ናችሁ፡፡
14ሁሉን ቻዩ በዚያ የነበሩትን ነገሥታት በበተነ ጊዜ፣ ከሰልሞን ተራራ እንደሚወርድ በረዶ አደረጋቸው፡፡
15አንተ ብርቱ የባሰን ተራራ ሆይ፤ እናንት ባለ ብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፣ እግዚአብሔር ሊኖርበት የመረጠውን ተራራ፣ በእርግጥ እግዚአብሔር ለዘላለም
16የሚኖርበትን ተራራ ለምን በምቀኝነት ትመለከቱታላችሁ?
17የእግዚአብሔር ሰረገላዎች እልፍ አእላፍ ነቸው ሺህ ጊዜም ሺህ ናቸው ጌታ በተቀደሰው ቦታ በሲና በመካከላቸው ነው፡፡
18ወደ ላይ ዐረግህ፣ ምርኮን አጋበስህ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ በዚያ ትኖር ዘንድ ከአንተ ጋር ከተዋጉት እንኳ ሳይቀር፣ ከሰዎች ስጦታን ተቀበልህ፡፡
19በየዕለቱ ሸክማችንን የሚሸከምልን መድኃኒታችን የሆነው እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ሴላ
20አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው ከሞት ሊታደገን የሚቻለው ጌታ ያህዌ ነው፡፡
21እግዚአብሔር የጠላቶችን ራስ በኃጢአታቸውም የሚጸኑትን ሰዎች ጠጉራም ዐናት ይፈነክታል፡፡
22ጌታ እንዲህ አለ፤ «ጠላቶቼን ከባሳን መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ ከባሕርም ጥልቅ አውጥቼ አመጣቸዋለሁ፤
23እግርህ በጠላትህ ደም እንዲጠልቅ የውሻህም ምላሽ ከጠላትህ ድርሻውን እንዲያገኝ ነው፡፡»
24አምላክ ሆይ፣ የክብር አካሄድህን፣ አምላኬና ንጉሤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያደርገውን የክብር አካሄድ አዩ፡፡
25የሚጫወቱ ከኋላ ሆነው ሲሄዱ መዘምራን ከፊት፤ መሣሪያ መካከላቸው ከበሮ የሚመቱ ደናግል ነበሩ፡፡
26እግዚአብሔርን በጉባኤ አመስግኑት በእውነት የእስራኤል ዘር የሆናችሁ ያህዌን አመስግኑት፡፡
27በመጀመሪያ በቁጥር ታናሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎችና ሰራዊቶቻቸው ታዩ፤ በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ፡፡
28እግዚአብሔር ሆይ፣ በቀድሞ ዘመን እንደዳረግኸው ኃይልህን ግለጥ
29ነገሥታት ስጦታቸውን ከሚያመጡልህ በኢየሩሳሌም ካለው ቤተ መቅደስህ ኃይልህን ግለጥ፡፡
30በሸምበቆ መካከል ያሉትን አራዊት ገሥጽ ኮርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጸቸው፡፡ አዋርዳቸው ስጦታዎች እንዲመጡልህም አድርጋቸው ጦርነትን የሚወዱ ሕዝቦችንም በትናችው፡፡
31መሳፍንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፡፡
32እናንት የምድር መንግሥታት ለያህዌ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፡፡ ሴላ
33ከጥንት ጀምሮ ከነበሩት ሰማያት በላይ ለሚራመደው በኃያል ድምፁ ለሚያስገመግመው ዘምሩ፡፡
34ግርማው በእስራኤል ላይ ኃይሉም በሰማያት ላይ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ኃይል ዐውጁ፡፡
35እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ በመቅደስህ ድንቅ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ ኃይልና ብርታት ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ይባረክ!
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።