1እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም ፊቱንም በላያችን ያብራ፡፡ ሴላ
2መንገድህ በምድር ላይ ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ፡፡
3እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝቦች ያመስግኑህ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ፡፡
4አንተ ለሕዝቦች ቅን ስለምትፈርድላቸው የምድር ሕዝቦችን ስለምትመራ ሕዝቦች ሁሉ ደስ ይበላቸው በእልልታም ይዘምሩ፡፡ ሴላ
5እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝቦች ያመስግኑህ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ፡፡
6ምድር ፍሬዋን ሰጠች አምላካችን እግዚአብሔር ባርኮናል፡፡
7እግዚአብሔር ባርኮናል የምድር ዳርቻዎች ሁሉ እርሱን ያከብሩታል፡፡