መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 66

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ
2ለስሙ ክብር ዘምሩ ምስጋናውን አድምቁ፡፡
3እግዚአብሔርን፣ «ሥራህ እንዴት ድንቅ ነው! ከኃይልህ ታላቅነት የተነሣ ጠላቶችህ ይገዙልሃል፡፡
4ምድር ሁሉ ያመልክሃል በዝማሬም ያመሰግኑሃል ለስምህም ይዘምራሉ» ባሉት፡፡ ሴላ
5ኑ የእግዚአብሔርን ሥራ እዩ ለሰው ልጆ ያደረገውስ አስፈሪ ነው፡፡
6ባሕሩን ደረቅ ምድር አደረገው ወንዙን በእግር ተሻገሩ እኛም እርሱ ባደረገው ነገር ደስ ብሎናል፡፡
7በኃይሉ ለዘላለም ይነግሣል ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፡፡ እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ፡፡ ሴላ
8ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔርን ባርኩ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ፡፡
9በሕያዋን መካከል አኑሮናል እግራችን እንዲንሸራተት አልፈቀደም፡፡
10እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ፈተንኸን ብር እንደሚፈተን እኛን ፈተንኸን
11ወደ ወጥመድ አገባኸን በጀርባችንም ከባድ ሸክም ጫንህብን፡፡
12ሰዎች ራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ በእሳትና በውሃ መካከል አለፍን የኃላ ኃላ ግን ወደ ሰፊ ስፍራ አመጣኸን፡፡
13የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ ቤትህ እመጣለሁ ስእለቴንም ለአንተ እከፍላለሁ፡፡
14ይህም መከራ በደረሰብኝ ጊዜ ከአፌ የወጣ፣ በከንፈሮቼም የተናገርሁት ስእለት ነው፡፡
15የሰቡ እንስሶችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ፣ እንዲሁም መዓዛው ደስ የሚያሰኝ የአውራ በግ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፡፡
16እናንት እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ኑና ስሙ፣ ለነፍሴ ያደረገላትን እነግራችኃለሁ፡፡
17በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤ በአንደበቴ አመሰገንሁት፡፡
18በውስጤ ኃጢአት ይዤ ቢሆን ኖሮ ጌታ አይሰማኝም ነበር፡፡
19አሁን ግን እግዚአብሔር በእርግጥ ሰምቶኛል ጸሎቴንም አድምጦአል፡፡
20ጸሎቴን ያልናቀ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።