መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 64

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሆይ፣ ድምፄን ስማ የብሶቴን ቃል አድምጥ፤ ከሚያስፈራ የጠላት ዛቻ ሕይወቴን አድናት
2ከክፉ አድራጊዎች ዐድማ ሰውረኝ ከዐመፀኞችም ሤራ አድነኝ፡፡
3እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ስለዋል መርዘኛ ቃላቸውንም እንደ ፍላጻ ያነጣጥራሉ
4ካሸመቁበት ቦታ ሆነው ንጹሑን ሰው ይነደፋታል ድንገት ይነድፉታል፤ አይፈሩምም፡፡
5ክፉ ዕቅድ ለማውጣት እርስ በርስ ይመካከራሉ፤ ወጥመድ ለመዘርጋትም በምስጢር ይነጋገራሉ፤ «ማንስ ሊያድን ይችላል?» ይባባላሉ፡፡
6እነርሱ ክፉ ዕቅድ አወጡ፤ በሐሳባቸውም፣ «በጥንቃቄ ዕቅድ አውጥተናል» ይላሉ፡፡ የሰው ሐሳብና ልብ በጣም ጥልቅ ነው፡፡
7እግዚአብሔር ግን በፍላጻው ይነድፋቸዋል እነርሱም በድንገት ይቆስላሉ፡፡
8በገዛ ምላሳቸው ያሰናክላቸዋል ጥፋትንም ያመጣባቸዋል የሚያዩአቸው ሁሉ በመገረም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ፡፡
9የሰው ልጆች ሁሉ ይፈራሉ የእግዚብሔር ያደረገውንም በይፋ ይናገራሉ፡፡
10ጻድቅ በያህዌ ደስ ይለዋል፤ እርሱንም መጠጊያው ያደርጋል ልበ ቅኖችም ሁሉ በእርሱ ይመካሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።