መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 63

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ! ከልቤ አንተን እሻለሁ ውሃ በሌለበት ደረቅና ጭው ያለ ምድረ በዳ ነፍሴ አንተን ተጠማች ሥጋዬም አንተን ናፈቀች፡፡
2ስለዚህ መቅደስህ ውስጥ አየሁህ ኃይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ፡፡
3ታማኝነትህ ከሕይወት ይበልጣልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል፡፡
4እንግዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ በስምህም እጆቼን አነሣሁ፡፡
5ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ ደስ እያለኝ የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ
6በመኝታዬ ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ፡፡
7አንተ ረዳቴ ነህና በክንፎችህ ጥላ ውስጥ ሐሤት አደርጋለሁ፡፡
8ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ብላለች ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፡፡
9ነፍሴን ማጥፋት የሚፈልጉ ግን ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤
10በሰይፍ ይገደላሉ ለቀበሮችም ምግብ ይሆናሉ፡፡
11ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል በእግዚአብሔ ስም የሚምሉ ሁሉ ይከብራ የሐሰተኞች አንደበትም ትዘጋለች፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።