መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 62

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ድነቴ የሚመጣው ከእርሱ ስለሆነ እግዚአብሔርን ብቻ በጸጥታ እጠብቃለሁ፡፡
2ዐለቴና መድኃኒቴ እርሱ ብቻ ነው መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም፡፡
3ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው? ይህን የዘመመ ግድግዳ የተንጋደደ ዐጥር ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትፈልጋላችሁ?
4እነርሱ የሚፈልጉት እርሱን ከክብሩ ለማዋረድ ስለሆነ በእርሱ ላይ ሐሰት መናገር ይወዳሉ፤ በአፋቸው ይመርቁታል፤ በልባቸው ግን ይረግሙታል፡፡ ሴላ
5እግዚአብሔርን ብቻ በጸጥታ እጠብቃለሁ
6ዐለቴና መድኃኒቴ እርሱ ብቻ ነው፡፡ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም፡፡
7ድነቴና ክብሬ ከእግዚአብሔር ነው እርሱ መጠጊያ ዐምባዬና መሸሸጊያ ነው፡፡
8ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ በፊቱም ልባችሁን አፍስሱ እግዚአብሔር ለእኛ መጠጊያችን ነውና፡፡ ሴላ
9ከዝቅተኛ ወገን መወለድ ከንቱ ነው፣ ከከፍተኛ ወገን መወለድም ሐሰት ነው ሚዛን ላይ ከፍ ብለው ቢታዩም ሁሉም በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው፡፡
10በዝርፊያ አትተማመኑ በቅሚያ በተገኘ ሀብትም ተስፋ አታድርጉ በዚህ አትበለጽጉምና ልባችሁ እነርሱ ላይ አታድርጉ፡፡
11እግዚአብሔር አንዴ ተናገረ እኔም ይህን ሁለቴ ሰማሁ፡፡ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፡፡
12ጌታ ሆይ፣ የኪዳን ታማኝነት የአንተ ነው አንተ ለእያንዳንዱ፣ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።