1እግዚአብሔር ሆይ፣ ጩኸቴን ስማ ጸሎቴንም አድምጥ፡፡
2ልቤ በዛለ ጊዜ ከምድር ዳርቻዎች ወደ አንተ እጣራለሁ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ፡፡
3አንተ መጠጊያዬ ከጠላትም የምከለልብህ ፅኑ ግንብ ሆነኸኛልና፡፡
4በማደሪያህ ለዘላለም ልኑር በክንፎችህም ጥላ ልከለል፡፡ ሴላ
5እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ስእለቴን ሰምተሃል ስምህን የሚያከብሩ ሰዎችን ርስት ለእኔ ሰጠህ፡፡
6የንጉሡን ዕድሜ አርዝመው ዘመኑንም እስከ ብዙ ትውልዶች ድረስ ጨምርለት፡፡
7ለዘላለም በእግዚአብሔር ፊት ይንገሥ፡፡
8ስእለቴን በየቀኑ እንድፈጽም ለስምህ ለዘላለም የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፡፡