መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 60

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሆይ፣ ጣልኸኝ፣ ሰባበርኸን፤ ተቆጣኸንም፤ አሁን ግን መልስህ አብጀኝ፡፡
2ምድሪቱን አናወጥኃት፣ ፍርክስክስ አደረግኃት፤ ተንገዳግዳለችና ስብራቷን ጠግን፡፡
3ሕዝብህን መከራውን አሳየኸው የሚያንገዳግድ ወይን ጠጅ እንድንጠጣም ሰጠኸን፡፡
4ከጠላት ቀስት እንዲያመልጡ ለሚፈሩህ ምልክት አደረግህላቸው፡፡ ሴላ
5የምትወደው ሕዝብህ ከጉዳት እንዲድን በቀኝህ ታደገን፤ መልስም ስጠን፡፡
6እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፣ «ሲኬምን እሸነሽናለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ አከፋፍላለሁ፡፡
7ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቁሬ፣ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው፡፡
8ሞዓብ መታጠቢ ገንዳዬ ነው፤ በኤዶም ላይ ጫማየን እወረውራለሁ ፍልስጥኤማውያን ላይ በድል እልል እላለሁ፡፡
9ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ያመጣኛል? ማንስ ወደ ኤዶም ይመራኛል?
10ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ፥ የጣልከን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አልወጣህም
11በጠላቶቻችን ላይ ድልን ስጠን የሰው ድጋፍ ከንቱ ነውና።
12በእግዚአብሔር እርዳታ ድል እንቀዳጃለን እርሱ ጠላቶቻችንን ከእግሩ በታች ይረግጣቸዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።