መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ በቁጣህ አትገሥጸኝ በመዐትህም አትቅጣኝ፡
2ያህዌ ሆይ፣ ደካማ ስለሆንሁ ምሕረት አድርግልኝ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተናውጠዋልና፣ ፈውሰኝ፡፡
3ነፍሴም ታወካለች፤ ያህዌ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ይቀጥላል?
4ወደ እኔ ተመለስ፤ አድነኝም፡፡ ከታማኝ ኪዳንህ የተነሣ አድነኝ
5በሞት የሚያስታውስህ የለም መቃብር ውስጥ ሆኖ፣ የሚያመሰግንህ ማን ነው?
6ከመቃተቴ የተነሣ ዝዬአለሁ ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ አልጋዬን በእንባ አርሳለሁ መኝታዬንም በእንባ አረጥባለሁ፡፡
7ከሐዘን የተነሣ ዐይኖቼ ፈዘዙ፤ ከባላጋራዎቼ የተነሣ ደከሙ፡፡
8እናንት ዐመፃን የምታደርጉ ሁሉ ከእኔ ራቁ ያህዌ የለቅሶዬን ድምፅ ሰምቷልና
9እንዲምረኝ ወደ እርሱ ያቀረብኩትን ልመና አድምጧል፤ ያህዌ ጸሎቴን ተቀብሏል፡፡
10ጠላቶቼ ሁሉ ይፈሩ፤ እጅግም ይታወኩ ወደ ኋላ ይመለሳሉ፤ በድንገትም ይዋረዳሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።