መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ ወደ አንተ ስጣራ ስማኝ መቃተቴንም አስብ፡፡
2ንጉሤና አምላኬ ወደ አንተ እጸልያለሁና የልመናዬን ጽምፅ አድምጥ
3ያህዌ ሆይ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ በማለዳ ልመናዬን ወደ አንተ አቀርባለሁ፤ እጠባበቃለሁም፡፡
4በእርግጥ አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም ክፉ ሰዎች ከአንተ አያድሩም፡፡
5እብሪተኛ በፊትህ አይቆምም ዐመፃን የሚያደርጉትህን ሁሉ ጠላህ፡፡
6ሐሰተኞችን ታጠፋለህ ደም የተጠሙትን አታላዮችን ያህዌ ይጸየፋል፡፡
7እኔ ግን በኪዳናዊ ታማኝነትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ በአክብሮት ፍርሃትም የተቀደሰ ማደሪያህ ውስጥ እሰግዳለሁ፡፡
8ጌታ ሆይ፣ በጠላቶች ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ መንገድህንም በፊቴ አቅና፡፡
9በአፋቸው እውነት የለም ልባቸው ተንኰለኛ ነው፡፡ ጉሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፡፡ በአንደበታቸው ይሸነግላሉ፡፡
10እግዚአብሔር ሆይ፣ የእጃቸውን ስጣቸው ተንኰላቸው መጥፊያቸው ይሁን! አንተ ላይ ዐምፀዋልና ከኃጢአታቸው ብዛት የተነሣ አስወግዳቸው፡፡
11በአንተ የተማመኑ ሁሉ ደስ ይበላቸው አንተ ከለላ ሁነሃቸዋልና ለዘላለም ሐሤት ያድርጉ፡፡ ስምህን የሚወዱ በአንተ ደስ ይበላቸው
12ያህዌ ሆይ፣ አንተ ጻድቁን ትባርካለህ እንደ ጋሻ በሞገስ ትከልላቸዋለህ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።