1እናንተ ገዢዎች እውነትን ትናገራላችሁ? እናንተ ሰዎች ቅን ፍርድ ትፈርዳላችሁ?
2የለም፤ በልባችሁ ክፋት ታውጠነጥናላችሁ በእጃችሁም በምድር ሁሉ ላይ በደል ትፈጽማላችሁ፡፡
3ክፉዎች በእናታቸው ማሕፀን እያሉ እንኳ ከመንገድ የወጡ ናቸው ሲወለዱ ጀምሮ የተሳሳቱና ውሸታሞች ናቸው፡፡
4መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው
5የአስማተኛውን ቃል አልሰማ እንዳለች እፉኝት ጆሮአቸውን ደፍነዋል፡፡
6እግዚአብሔር ሆይ፣ ጥርሳቸውን አፋቸው ውስጥ ስበር የአንበሶችንም መንጋጋ አውላልቅ፡፡
7ፈስሶ እንደሚያልቅ ውሃ ይጥፉ የቀስታቸው ፍላጻ ዱልዱም ይሁን፡፡
8እየሄደ ሟምቶ እንደሚጠፋ ቀንድ አውጣ፣ ፀሐይ እንደማያይም ጭንጋፍ ይሁኑ፡፡
9የሚነደው እሾኽ እሳት ገና ድስታችሁን ሳያሞቀው እርጥቡንም ደረቁንም እኩል በዐውሎ ነፋስ ጠራርጐ ይወስዳቸዋል፡፡
10ጻድቃን የእግዚአብሔርን በቀል ሲያዩ ደስ ይላቸዋል እግሩንም በግፈኞች ደም ይታጠባል፡፡
11በዚህ ጊዜ ሰዎች፣ «በእርግጥ ለጻድቃን ዋጋ አላቸው፤ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ» ይላሉ፡፡