መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 57

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሆይ ማረኝ አቤቱ ማረኝ የመከራው ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና፡፡ ጥፋት እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ እጠለላለሁ፡፡
2ወደ ልዑል እግዚአብሔር የሚያስፈልገኝን ሁሉ ወደሚሰጠኝ አምላክ እጮኻለሁ፡፡
3ከሰማይ ልኮ ያድነኛል የሚያስጨንቁኝንም ያዋርዳቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይልካል፡፡
4ነፍሴ በአንበሶች ተከባለች፣ ሊውጡኝ በተዘጋጁ መካከል ወድቄአለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ ምሳቸውም የተሳለ ሰይፍ ነው፡፡
5እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ይስፋፋ
6ለእግሬ ወጥመድ ዘረጉ፣ ነፍሴንም አጐበጡአት፤ መንገዴ ላይ ጉድጓድ ቆፈሩ፤ ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት፡፡ ሴላ
7ልቤ ጽኑ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ ልቤ ጽኑ ነው እቀኛለሁ፤ እዘምራለሁ፡፡
8ነፍሴ ሆይ፣ ንቂ በገናና መሰንቆም ተነሡ እኔም በማለዳ እነሣለሁ፡፡
9ጌታ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ በመንግሥታት መካከል ምስጋና እዘምራለሁ፡፡
10ዘላለማዊ ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው ታማኝነትህም እስከ ደመናት ይደርሳል፡፡
11እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ በል ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ይስፋፋ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።