መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 56

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሆይ፣ ሰዎች ስለሚያጠቁኝና ጠላቶቼም ቀኑን ሙሉ ስለሚያሳድዱኝ ማረኝ፡፡
2ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ በእብሪት የሚዋጉኝ ብዙ ናቸውና፡፡
3እኔ ግን ፍርሃት ሲይዘኝ እምነቴን አንተ ላይ አደርጋለሁ
4ቃሉን በማመሰግው አምላክ በእግዚአብሔር ታምኛሁና አልፈራም ከቶ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
5ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምማሉ ሐሳባቸው ሁሉ እኔን መጉዳት ነው፡፡
6ይዶልታሉ፤ ያደባሉ ሕይወቴ ላይ እንደሚያደቡት ሁሉ ርምጃዬንም ይከታተላሉ፡፡
7አምላክ ሆይ፣ በምንም መንገድ እንዲያመልጡ አታድርጋቸው፤ በቁጣህ ሕዝቦችን አዋርዳቸው፡፡
8የመንከራተት ቀኖቼን ቆጥረሃል እንባዎቼን በመያዣህ አኑረሃል፡፡ ሁሉስ በመጽሐፍህ ያለ አይደለምን?
9ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑን በእርግጥ ዐወቅሁ፡፡
10ቃሉን በማመሰግነው አምላክ ቃሉን በማመመሰግነው ያህዌ
11በአምላክ ታምኛለሁና አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
12አምላኬ ሆይ፣ የተሳልሁትን እፈጽማለሁ ለአንተም የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፡፡
13ነፍሴን ከሞት፣ እግሬን ከመሰናከል አድነሃልና በሕያዋን ብርሃን፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።