1ኃያል ሆይ፣ ሁከት በመፍጠር ለምን ትኩራለህ? የእግዚአብሔር ኪዳን ታማኝነት ዕለት ዕለት ነው፡፡
2አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ ጥፋትን ያውጠነጥናል፡፡
3ከመልካም ይልቅ ክፋትን፣ እውነትን ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ወደድህ፡፡
4አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፣ ሌሎችን የሚያጠፋ ቃል ወደድህ፡፡
5ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ያጠፋሃል ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤ ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል፡፡
6ጻድቃን ይህን ዐይተው ይፈራሉ እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤
7«ተመልከቱ፣ እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣ ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ በክፋቱም የበረታ ያ ሰው እነሆ!»
8እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ የወይራ ዛፍ ነኝ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ በእግዚአብሔር ምሕረት እታመናለሁ።
9ስላደረግኸው ነገር ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤ ስምህ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ በቅዱሳንም መካከል አመሰግንሃለሁ።