መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 53

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሞኝ በልቡ፣ «እግዚአብሔር የለም» ይላል ብልሹዎች ናቸው፤ ጸያፍ ነገርም አድርገዋል መልካም የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም፡፡
2አስተዋዮችና እርሱን የሚፈልጉ ሰዎች ለማግኘት፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ፡፡
3ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር ብለዋል፤ በአንድነትም ብልሹዎች ሆነዋል፡፡ መልካም የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም፡፡
4ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን እንጀራ እንደሚበላ ሰው ሕዝቤን የሚበሉ፣ እግዚአብሔርንም ጠርተው የማያውቁት ሰዎች አይማሩምን?
5ምንም የሚያስፈራ ነገር ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤ የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት እግዚአብሔር በተነ፤ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው እንዲህ ያሉ ሰዎች ያፍራሉ፡፡
6ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በመጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከምርኮ በመለሰ ጊዜ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፤ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል!
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።