መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 51

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ርኅራኄም ብዛት መተላለፌን ደምስስ፡፡
2በደሌን ፈጽሞ እጠብልኝ ከኃጢአቴም አንጻኝ፡፡
3መተላለፌን ዐውቃለሁና ኃጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው፡፡
4አንተን፣ በእርግጥ አንተን ብቻ በደልሁ ስትናገር ትክክል ነህ፤ ስትፈርድም ትክክል ነህ፡፡
5ስወለድ ጀምሮ በደለኛ ነህ ገና እናቴም ስትወልደኝ ኃጢአተኛ ነኝ፡፡
6እነሆ፣ አንተ ልቤ ውስጥ እውነትን ትሻለህ ስለዚህ ጥልቅ ጥበብን በውስጤ አስተምረኝ፡፡
7በሂሶጵ እርጨኝ እኔም እነጻለሁ፡፡ እጠበኝ፤ ከበረዶም ይልቅ እነጻለሁ፡፡
8ያደቀቅሃቸው አጥንቶቼ ደስ እንዲላቸው ደስታንና ሐሤትን አሰማኝ፡፡
9ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፣ በደሌን ሁሉ ደምስስልኝ፡፡
10አምላኬ ሆይ፣ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ
11ከፊትህ አትጣለኝ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድብኝ፡፡
12የማዳንህን ደስታ መልስልኝ በእሺታ መንፈስም ደግፈኝ ያዘኝ፡፡
13በዚያ ጊዜ፣ ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ፡፡ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ፡፡
14የድነቴ አምላክ ሆይ፣ ደም አፍሳሽነቴን ይቅር በል አንደበቴም በደስታ ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል፡፡
15ጌታ ሆይ፣ ከንፈሮቼን ክፈት አፌም ምስጋናህን ያውጃል፡፡
16መሥዋዕትን ብትወድ ኖሮ፣ እሰጥህ ነበር፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ደስ አያሰኝህም፡፡
17የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው አንተ፣ የተሰበረውን የተዋረደውን መንፈስ አትንቅም፡፡
18በበጐነትህ ለጽዮን መልካም አድርግ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች ሥራ፡፡
19በዚያ ጊዜ የጽድቅ መሥዋዕት፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና ፈጽሞ የሚቃጠል መሥዋዕት ደስ ያሰኝሃል፡፡ እኛም በመሠዊያህ ላይ እንደ ገና ኮርማዎችን እናቀርባለን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።