መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የጽድቄ አምላክ ሆይ፣ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ ከጭንቀቴም አሳርፈኝ ማረኝ ጸሎቴንም ስማ፡፡
2እናንተ ሰዎች እስከ መቼ ክብሬን ታወርዳላችሁ? እስከ መቼ ከንቱ ነገር ትወዳላችሁ፤ ሐሰትንስ ትፈልጋላችሁ? ሴላ
3ያህዌ ጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ ዕወቁ፡፡ በጠራሁት ጊዜ ያህዌ ይሰማኛል፡፡
4የቱንም ያህል ብትፈሩ ኃጢአት አትሥሩ! በመኝታችሁ እያላችሁ በልባችሁ አሰላስሉ፤ ጸጥም በሉ፡፡ ሴላ
5ለያህዌ የጽድቅ መሥዋዕት አቅርቡ እምነታችሁንም እርሱ ላይ አድርጉ፡፡
6ብዙዎች፣ «መልካሙን ማን ያሳየናል?» ይላሉ፡፡ ያህዌ ሆይ፣ የፊትህን ብርሃን እኛ ላይ አብራ፡፡
7ብዙ እህልና ወይን ካገኙ ሰዎች ይበልጥ አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል፡፡
8በሰላም የምታኖረኝ አንተ ብቻ ስለሆንህ በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።