መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 49

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሕዝቦች ሁሉ ይህን ስሙ በዓለም የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ፡፡
2ዝቅተኞችና ከፍተኞች ሀብታሞችና ድኾች ይህን በአንድነት አድምጡ፡፡
3አፌ ጥበብን ይናገራል የልቤ ሐሳብም ማስተዋልን ይሰጣል፡፡
4ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ በበገናም የምሳሌዎቹን ትርጒም እገልጣለሁ፡፡
5ክፉ ቀን ሲመጣና አታላዮች ሲከብቡኝ ለምን እፈራለሁ?
6በሀብታቸው የሚመኩትንና በብልጽግናቸው የሚተማመኑትን ለምን እፈራለሁ?
7ማንም ወንድሙን መቤዠት ለእርሱም ቤዛ የሚሆነውን ዋጋ ለእግዚአብሔር መክፈል አይችልም፡፡
8የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና በቂ ዋጋ ሊገኝለት አይችልም፡፡
9እንዳይሞትና ወደ መቃብር እንዳይወርድ ማንም ለዘላለም መኖር አይችልም፡፡
10ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ፤ ጠቢባን እንኳ ከሞኞችና ከሞኞች እኩል በአንድት ይጠፋሉ ሀብታቸውንም ለሌላው ጥለው ይሄዳሉ፡፡
11እነርሱ የሚያስቡት ቤተ ሰባቸው ለዘላለም እንደሚኖር፣ መኖሪያ ስፍራቸውም ለትውልድ ዘመን እንደማይጠፋ በመሆኑ መሬቶቻቸውን በስማቸው ይሰይማሉ፡፡
12ግን ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም አሁን ታይተው በኃላ እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል፡፡
13ይህ የምኞት ዕድል ፈንታ የእነርሱንም አባባል የሚከተሉ ሰዎች መጨረሻ ግብ ነው፡፡
14እንደ በጐች ለሞት የተመደቡ ናቸው እረኛቸውም ሞት ነው በማለዳ ቅኖች ይገዟቸዋል፤ መኖሪያ ቦታ አጥቶ አካላቸው ሲኦል ውስጥ ይፈራርሳል፡፡
15እግዚአብሔር ግን ሕይወቴን ከሲኦል ኃይል ይቤዣል፤ እርሱም ይቀበለኛል፡፡ ሴላ
16ሰው ባለጠጋ ቢሆን፣ የቤቱም ክብር ቢበዛለት አትፍራ፡፡
17በሚሞትበት ጊዜ ምንም ይዞ አይሄድም ክብሩም አብሮት አይወርድም፡፡
18ሰው በሕይወቱ ዘመን ቢደሰትም፣ ሁሉም ነገር ስለ ተሳካለት ቢመሰገንም፣
19በሞት ተለይቶ ከእንግዲህ ብርሃን ወደሚያይበት ወደ አባቶች ትውልድ ይሄዳል፡፡
20ሁሉም ነገር እያለው ማስተዋል የጐደለው ሰው ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።