መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 48

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ታላቅ ነው፣ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰ ተራራው ላይ ከፍ ያለ ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል፡፡
2የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው፡፡
3እግዚአብሔር በቤተ መንግሥት ውስጥ ሆኖ ብርቱ ምሽጓ መሆኑን አስመስክሮአል፡፡
4እነሆ፣ ነገሥታት ተባብረው መጡ በአንድነትም ገሠገሡ፡፡
5ዐይተው ተደነቁ ደንግጠውም ፈረጠጡ፡፡
6በዚያ ፍርሃትና ድንጋጤ ያዛቸው ምጥ እንደያዛት ሴት ብርክ ያዛቸው፡፡
7የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር አንተ አንበረከክሃቸው
8በጆሮአችን እንደ ሰማን በሰራዊት አምላክ ከተማ በአምላካችን ያህዌ ከተማ በዐይናችን አየን፡፡
9አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሆነን ታማኝነትህን እናስባለን፡፡
10እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ስምህ ምስጋናህም እስከ ምድር ዳርቻ ነው፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት፡፡
11ስለ ጽድቅህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበላት የይሁዳም ልጅ ሐሤት ታድርግ፡፡
12በጽዮን ተራራ፣ በዙሪያዋም ተመላለሱ፣ ማማዎቿን ቁጠሩ፤
13ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ ጠንካራ ቅጥሮቿን አስተውሉ ምሽጐችዋንም ተመልከቱ፡፡
14ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነው፤ እስከ መጨረሻው መሪያዎችንም እርሱ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።