መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 47

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሕዝቦች ሁሉ እጆቻችሁን አጨብጭቡ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፡፡
2በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ የሆነው ልዑል ያህዌ እጅግ አስፈሪ ነው፡፡
3ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፣ መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን፡፡
4ለሚወደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን ርስታችንን እርሱ መረጠልን፡፡
5እግዚአብሔር በእልልታ፣ ያህዌም በመለከት ድምፅ ዐረገ
6ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ
7እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ስለዚህ በማስተዋል ዘምሩለት፡፡
8እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ነግሦአል እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል፡፡
9ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ የምድር ነገሥታት የእግዚአብሔር ናቸውና እርሱ እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።