መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 46

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን፣ በመከራም ቀን ረዳታችን ነው፡፡
2ስለዚህ ምድር ብትናወጥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ፣ አንፈራም፡፡
3ውሆች ቢያስገመግሙ፣ ዐረፋ ቢደፍቁም፣ ከውሃው ሙላት የተነሣ ተራሮች ቢንቀጠቀጡም አንደነግጥም፡፡ ሴላ
4የእግዚአብሔርን ከተማ የልዑልንም የተቀደሰ ማደሪያ ደስ የሚያሰኙ ወራጅ ወንዞች አሉ፡፡
5እግዚአብሔር በመካከሏ ነውና አትናወጥም ጠዋት በማለዳ እግዚአብሔር ይረዳታል፡፡
6ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታት ወደቁ ድምፁን ከፍ አድርጐ አሰማ ምድርም ቀለጠች፡፡
7የሰራዊት ጌታ ያህዌ ከእኛ ጋር ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው፡፡ ሴላ
8ኑ የእግዚአብሔርን ሥራ በምድር ላይ የደረሰውን ጥፋት ተመልከቱ፡፡
9ከምድር ዳር እስከ ዳርቻ ጦርነትን ያስወግዳል ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርንም ያነክታል ጋሻዎችንም በእሳት ያቃጥላል፡፡
10ጸጥ በሉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ፡፡
11የሰራዊት አምላክ ያህዌ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው፡፡ ሴላ
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።