1አምላክ ሆይ፣ ፍረድልኝ ከጽድቅ ከራቀ ሕዝብ ጋር ተሟገትልኝ፡፡
2አምላክ ሆይ፣ አንተ ብርታቴ ነህ ለምን ተውኸኝ? ጠላት እያስጨነቀኝ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?
3ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እኔንም ይምሩኝ፡፡ ወደ ቅዱስ ኮረብታህና ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ፡፡
4እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ እሄዳለሁ ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላኬ አቀናለሁ፡፡ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ በበገና አመሰግንሃለሁ፡፡
5ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡