መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 41

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ለድኾች የሚያስብ ቡሩክ ነው እርሱንም በመከራ ቀን ያህዌ ያድነዋል፡፡
2ያህዌ ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል በምድርም ላይ ይባርከዋል ለጠላቶቹ ምኞትም አሳልፎ አይሰጠውም፡፡
3ታሞ በተኛበት አልጋ ያህዌ ይንከባከበዋል በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል፡፡
4እኔም፣ «ያህዌ ሆይ፣ ማረኝ! በአንተ ላይ ኃጢአት አድርጌአለሁና ፈውሰኝ» አልሁ፡፡
5«የሚሞተው መቼ ነው፤ ስሙ የሚደመሰሰውስ መቼ ነው?» እያሉ ጠላቶቼ እኔ ላይ ክፉ ይናገራሉ፡፡
6ሊጠይቀኝ ቢመጣ እንኳ በልቡ ስድብ እያመቀ ከአንገት በላይ ይናገራል ወጥቶም ወሬ ይነዛል፡፡
7ጠላቶቼ ሁሉ ተባብረው እኔ ላይ ያሾኮሽካሉ የክፋ ነገርም በላዬ ያውጠነጥናሉ
8«ክፉ ደዌ ይዞታል፤ አልጋ ላይ ወድቋል ከእንግዲህ ከተኛበት አይነሣም» ይላሉ።
9እንጀራዬን ተካፍሎ የበላ የተማመንሁበት የቅርብ ወዳጄ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ፡፡
10አንተ ግን ያህዌ ሆይ ማረኝ፤ የእጃቸውን እንድሰጣቸውም አስነሣኝ፡፡
11ጠላቴ በእኔ ላይ ድል አላገኘምና እንደ ወደድከኝ በዚህ ዐወቅሁ፡፡
12ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ፡፡
13የእስራኤል አምላክ ያህዌ ከዘላለም እስከ ዘለላለም ይመስገን፡፡ አሜን አሜን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።