መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የተነሡ ብዙዎች ናቸው፡፡
2ብዙ ሰዎች፣ «እግዚአብሔር አያድነውም» እያሉ ስለ እኔ ይናገራሉ፡፡
3አንተ ግን ያህዌ ሆይ፣ ዙሪያዬን እንደ ጋሻ ትከልለኛለህ፣ ክብሬንና ራሴንም ከፍ የምታደርግ አንተ ነህ፡፡
4ድምፄን ወደ ያህዌ አነሣለሁ እርሱም ከተቀደሰው ተራራው ይመልስልኛል፡፡ ሴላ
5በሰላም እተኛለሁ፤ እንቀላፋለሁ ያህዌ ስለ ጠበቀኝ ከእንቅልፌ ተነሣሁ፡፡
6በየአቅጣጫው ከተነሡብኝ ሰዎች ብዛት አልፈራም፡፡
7ያህዌ ሆይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ አድነኝ! አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መታህ የክፉዎችን ጥርስ ሰበርህ፡፡
8መዳን ከያህዌ ነው በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።