መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 39

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እኔ፣ «በአንደበቴ እንዳልበድል ለምናገረው እጠነቀቃለሁ፣ በክፉዎችም ፊት እስካለሁ ድረስ፣ በአፌ ልጓም አደርጋለሁ» አልሁ፡፡
2አንድ ቃል እንኳ ሳልናገር ዝም አልሁ ለመልካም ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤ ያም ሆኖ ጭንቀቴ ባሰ፡፡
3ልቤ በውስጤ ጋለ ስለ እነዚህ ነገሮች ሳስብ እንደ እሳት ነደደ፡፡ ከዚያም መናገር ጀመርሁ፡፡
4«ያህዌ ሆይ፣ የሕይወቴ መጨረሻ መቼ እንደ ሆነና የዕድሜዬን ልክ አሳውቀኝ አላፊ ጠፊ መሆኔን አሳየኝ፡፡
5እነሆ፣ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አኖርህ ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፡፡ በእርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ጥላ ነው፡፡ ሴላ
6በእርግጥ ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመላለሳል፡፡ ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል፡፡
7ጌታ ሆይ፣ አሁንስ ማንን ልጠብቅ? ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ፡፡
8ከኃጢአቴ አድነኝ የሞኞች መዘባበቻ አታድርገኝ፡፡
9ይህን ያደረግህ አንተ ነህና ዝም እላለሁ አፌንም አልከፍትም፡፡
10ክንድህን አንሣልኝ ከእጅህ ምት የተነሣ ዝዬአለሁ፡፡
11ሰውን በኃጢአቱ ትገሥጸዋለህ፤ ትቀጣዋለህም የሚወደውንም ነገር እንደ ብል ታጠፋበታለህ፡፡ በእርግጥ ሰው ሁሉ ተን ነው፡፡ ሴላ
12ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ ለቅሶየንም ቸል አትበል፡፡ በአንተ ፊት እንደ መጻተኛ ነኝና እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ፡፡
13ከመሞቴ በፊት ዳግመኛ ደስ እንዲለኝ ዐይንህን ከላዬ አንሣ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።