1ያህዌ ሆይ፣ በቁጣህ አትገሥጸኝ በመዓትህም አትቅጣኝ፡፡
2ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና እጅህ ተጭናኛለች፡፡
3ከቁጣህ የተነሣ መላው አካሌ ታመመ ከኃጢአቴ የተነሣም ዐጥንቶቼ ጤና የላቸውም፡፡
4በደሌ ውጦኛል እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል፡፡
5በሞኝነት ካደረግሁት የተነሣ ቁስሌ መገለ፤ ሸተተም፡፡
6ጐበጥሁ፤ በየቀኑም እያጐነበስኩ ሄድሁ ቀኑን ሙሉ በትካዜ ዋልሁ፡፡
7ውስጤ እንደ እሳት ይቃጠላል ሥጋዬም ጤና የለውም፡፡
8እንደ ዲዳ ሆንሁ፤ ፈጽሞም ደቀቅሁ ከልቤ ምሬት የተነሣ እቃትታለሁ፡፡
9ጌታ ሆይ፣ የጥልቅ ልቤን ናፍቆት አንተ ታውቃለህ መቃተቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም፡፡
10ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበት ከድቶኛል የዐይኔም ብርሃን ፈዝዞአል፡፡
11ካለሁበት ሁኔታ የተነሣ፣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ ጐረቤቶቼም ርቀው ቆሙ፡፡
12ሕይወቴን ማጥፋት የሚወዱ ወጥመድ ዘረጉብኝ ሊጐዱኝ የሚፈልጉም በዛቻ ተናገሩኝ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ፡፡
13እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ ምንም መናገር እንደማይችል ዲዳ ሰው ሆንሁ፡፡
14ጆሮው እንደማይሰማ አንደበቱም መልስ መስጠት እንደማይችል ሰው ሆንሁ፡፡
15ያህዌ ሆይ፣ በፍጹም ልቤ አንተን እጠብቃለሁ ጌታ ሆይ፣ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ፡፡
16ይህን የምለው ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዳይላቸው ነው፤ እግሬ ቢንሸራተት ክፉ ነገር ያደርጉብኛል፡፡
17ልወድቅ ተቃርቤአለሁ ሕመሜም ፋታ አልሰጠኝም፡፡
18በደሌን እናዘዛለሁ ኃጢአቴም አስጨንቆኛል፡፡
19ጠላቶቼ እጅግ ብዙ ናቸው ያለ ምክንያት የሚጠሉንም በዝተዋል፡፡
20በመልካም ፈንታ ክፉ መለሱልኝ መልሙን እየተከተልሁ ቢሆንም፣ እነርሱ ግን እኔ ላይ የሐሰት ክስ ደረደሩ፡፡
21ያህዌ ሆይ፣ አትተወኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ
22ጌታ መድኃኒቴ እኔን ለመርዳት ፍጠን፡፡