መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 36

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ክፉ ሰው በልቡ፣ ክፋትን ያስባል በዐይኖቹም ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም፡፡
2በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ እያሰበ ራሱን ይሸነግላል፡፡
3ንግግሩ ተንኰልንና ሐሰትን የተሞላ ነው፤ አስተዋይ መሆንንና መልካም ማድረግን አይፈልግም፡፡
4በመኝታው ላይ ክፋት ያውጠነጥናል ራሱን ወደ ክፉ መንገድ ይመራል ክፉውንም ነገር አያርቅም፡፡
5ያህዌ ሆይ፣ ታማኝነትህ እስከ ሰማይ እውነተኛነትህም እስከ ደመናት ይደርሳል፡፡
6ጽድቅህ እንደ እግዚአብሔር ተራራ ነው ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ ያህዌ ሆይ፣ አንተ ሰውንም እንስሳንም ትጠብቃለህ፡፡
7እግዚአብሔር ሆይ፣ ታማኝነትህ እንዴት ክቡር ነው! የሰው ልጆች ሁሉ በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ፡፡
8ከቤትህ ሲሳይ ተመግበው ይጠግባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ፡፡
9በአንተ ዘንድ የሕይወት ምንጭ አለ በአንተ ብርሃን ብርሃን እናያለን፡፡
10ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ አይቋረጥባቸው፡፡
11የእብሪተኛ እግር አይቅረበኝ የክፉ ሰው እጅም አያሳድደኝ፡፡
12ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁ መነሣትም እንደማይችሉ ተመልከት፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።