1ያህዌን ሁልጊዜ አመሰግናለሁ ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው፡፡
2ያህዌን አመሰግናለሁ! ትሑታን ይህን ሰምተው ደስ ይበላቸው፡፡
3ያህዌን ከእኔ ጋር አመስግኑት በአንድነት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ፡፡
4ያህዌን ፈለግሁ እርሱም መለሰልኝ ከፍርሃቴም ሁሉ አዳነኝ፡፡
5ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ ፊታቸውም በፍጹም አያፍርም፡፡
6ይህ ችግረኛ ጮኸ እግዚአብሔርም ሰማው ከመከራውም ሁሉ አዳነው፡፡
7የያህዌ መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸዋልም፡፡
8ያህዌ መልካም መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፡፡ በእርሱ የተማመነ ሰው ቡሩክ ነው፡፡
9እናንተ ቅዱሳን ያህዌን ፍሩ እርሱን የሚፈሩ አንዳች አያጡምና፡፡
10አንበሶች ሊያጡ ሊራቡም ይችላሉ ያህዌን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም፡፡
11ልጆቼ ሆይ፣ ኑ ስሙኝ ያህዌን መፍራት አስተምራችኋለሁ፡፡
12ሕይወትን የሚወድ፣ መልካም ነገርን ለማየት ረጅም ዕድሜ የሚፈልግ ማነው?
13እንግዲያስ አንደበትህን ከክፉ ከልክል ከንፈርህንም ከውሸት ጠብቅ፡፡
14ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ ሰላምን ፈልጋት ደግሞም ተከተላት፡፡
15የያህዌ ዐይኖች ጻድቃን ላይ ናቸው፡፡ ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ተከፍተዋል፡፡
16መታሰቢያቸውን ከምድር ላይ ለማጥፋት የያህዌ ፊት ክፉ በሚያደርጉ ላይ ነው።
17ጻድቃን ወደ ያህዌ ይጮኻሉ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል፡፡
18ያህዌ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል፡፡
19የጻድቅ መከራው ብዙ ነው ያህዌ ግን ከሁሉም ያድነዋል፡፡
20ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም፡፡
21ኃጢአተኛን ክፋት ይገድለዋል ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈርድባቸዋል፡፡
22ያህዌ የባርያዎቹን ነፍስ ይታደጋል እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም፡፡