መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 33

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ጻድቃን ሆይ፣ በያህዌ ደስ ይበላችሁ ቅኖች ሊያመሰግኑት ይገባል፡፡
2ያህዌን በመሰንቆ አመስግት ዐሥር አውታር ባለው በገና ዘምሩለት፡፡
3አዲስ ዝማሬ አቅርቡለት ባማረ ቅኝት በገና ደርድሩ፤ እልልም በሉ፡፡
4የያህዌ ቃል እውነት ነው ሥራውም ሁሉ የታመነ ነው፡፡
5እርሱ ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል ምድር በያህዌ ኪዳን ታማኝት ተሞልታለች፡፡
6ያህዌ ሰማያትን በቃሉ የሰማይ ሰራዊትን በአፉ እስትንፋስ ፈጠረ፡፡
7የባሕርን ውሆች እንደ ክምር ቀላዩንም በመከማቻ ስፍራ አኖረ፡፡
8ምድር ሁሉ ያህዌን ትፍራው በዓለም ያሉ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ፡፡
9እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤ እርሱ አዞአልና በስፍራቸው ጸኑ፡፡
10ያህዌ የሕዝቦችን ምክክር ያጨናግፋል ዕቅዳቸውንም ከንቱ ያደርጋል፡፡
11የያህዌ ዕቅድ ግን ለዘላለም ይኖራል የልቡም ሐሳቡም ለትውልድ ሁሉ ነው፡፡
12ያህዌ አምላኩ የሆነለት፣ ርስቱ እንዲሆን የመረጠውም ሕዝብ ቡሩክ ነው፡፡
13ያህዌ ከሰማይ ይመለከታል የሰው ልጆችንም ሁሉ ያያል፡፡
14ከማደሪያው ሆኖ፣ በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ይመለከታል፡፡
15የሁሉንም ልብ የሠራ እርሱ ነው የሚያደርጉትንም ሁሉ ይመለከታል፡፡
16ንጉሥ በሰራዊቱ ብዛት አይድንም፤ ጀግናም በኃይሉ ብርታት አያመልጥም፡፡
17በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤ በብርቱ ጉልበቱም ማንም አይድንም
18እነሆ፣ የያህዌ ዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤ በኪዳን ታማኝነቱ በሚታመኑት ላይ አትኩረዋል፡፡
19ይህም የሚሆነው ከሞት ሊያድናቸውና ከራብ ዘመንም ሊጠብቃቸው ነው፡፡
20ያህዌን በተስፋ እንጠብቃለን እርሱ ረድኤታችንና ጋሻችን ነው፡፡
21በቅዱስ ስሙ ተማምነናልና ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋል፡፡
22ያህዌ ሆይ፣ ተስፋችንን አንተ ላይ አድርገናልና ምሕረትህ በእኛ ላይ ይሁን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።