1ያህዌ ሆይ፣ አንተ አንሥተኸኛልና ጠላቶቼም በእኔ ላይ ደስ እንዲላቸው አላደረግህምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፡፡
2ያህዌ ሆይ፣ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ጮኽሁ አንተም ፈውሰኸኝ፡፡
3ያህዌ ሆይ፣ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ወደ መቃብር ከመውረድም አዳንኸኝ፡፡
4እናንት የእርሱ ታማኝ ሕዝቦች ለያህዌ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፤ ቅድስናውን ስታስታውሱ፣ ውዳሴ ስጡ፡፡
5ቁጣው ለአጭር ጊዜ ነው ሞገሱ ግን ለዕድሜ ልክ ነው፡፡ ሌሊት ሲለቀስ አድሮ ማለዳ ደስታ ይሆናል፡፡
6በልበ ሙሉነት «አልናወጥም!» አልሁ፡፡
7ያህዌ ሆይ በሞገስህ እንደ ተራራ ብርቱ አደረግኸኝ ፊትህን ስትሰውር ግን ውስጤ ታወከ፡፡
8ያህዌ፣ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ከጌታም ዘንድ ሞገስ ፈለግሁ፡፡
9እኔ ብሞት፣ ወደ መቃብርም ብወርድ ምን ጥቅም አለው? አፈር ያመሰግንሃልን? ታማኝነትህንስ ይናገራልን?
10ያህዌ ሆይ፣ ስማኝ ማረኝም፣ ያህዌ ረዳት ሁነኝ፡፡
11ዋይታዬን ወደ ሽብሸባ ለወጥህልኝ ማቄን አስወግደህ ደስታን አለበስከኝ፡፡
12እንግዲህ፣ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፡፡ አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፡፡