1እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ለያህዌ ምስጋና ስጡ ስለ ክብሩና ስለ ብርታቱ ለያህዌ ምስጋና ስጡ፡፡
2ለስሙ የሚገባውን ክብር ለያህዌ ስጡ በቅድስናው ውበት ለያህዌ ስገዱ
3የያህዌ ድምፅ በውሆች ላይ ያስተጋባል የክብር አምላክ ያንጐዳጉዳል ያህዌ በብዙ ውሆች ላይ ድምፁን ያሰማል፡፡
4የያህዌ ድምፅ ኃያል ነው የያህዌ ድምፅ ባለ ግርማ ነው፡፡
5የያህዌ ድምፅ የሊባኖስን ዝግባ ይሰብራል
6ሊባኖን እንደ ጥጃ፣ ስርዮንን እንደ ኮርማ ያዘልላል፡፡
7የያህዌ ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል
8የያህዌ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል የያህዌ ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል፡፡
9የያህዌ ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል ጫካዎችን ይመነጥራል፡፡ ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ፣ «ክብር!» ይላል፡፡
10ያህዌ በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል ያህዌ ለዘላለም ይነግሣል፡፡
11ያህዌ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል ያህዌ ሕዝቡን በሰላም ይባርካል፡፡