1አሕዛብ ለምን ያሤራሉ? ሕዝቦችስ ለምን በከንቱ ያድማሉ?
2የምድር ነገሥታት በአንድነት ተነሡ ገዦችም በአንድነት አሤሩ እንዲህ በማለትም በያህዌና በመሲሑ ላይ አሤሩ
3«እግር ብረታቸውን ከእግራችን እንቁረጥ፣ ሰንሰሰታቸውንም በጥሰን እንጣል፡፡»
4በሰማያት የሚቀመጥ እርሱ ያፌዝባቸዋል ጌታም ይሳለቅባቸዋል፡፡
5ከዚያም በቁጣው ያናግራቸዋል እንዲህ በማለትም በመዐቱ ያስፈራቸዋል
6«እኔ ራሴ በጽዮን፣ በተቀደሰውም ተራራዬ ንጉሤን ሾምሁ፡፡»
7የያህዌን ዐዋጅ ዐውጃለሁ፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ፣ «አንተ ልጄ ነህ! በዚህ ቀን አባትህ ሆኛለሁ፡፡
8ለምነኝ፤ አሕዛብን ለርስትህ የምድር ነገሥታትንም ለግዛትህ እሰጥሃለሁ፡፡
9በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ ሸክላ ሠሪው እንዳበጀው ዕቃ ታደቃቸዋለህ፡፡»
10ስለዚህ አሁን እናንት ነገሥታት ተጠንቀቁ እናንት የምድር ገዦች አስተውሉ፡፡
11ያህዌን በፍርሃት አምልኩት በመንቀጥቀጥ ተገዙለት፡፡
12እንዳይቆጣ በመንገድም እንዳትጠፉ ልጁን ሳሙት፡፡ ቁጣው ፈጥኖ ይነዳልና፡፡ እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው፡፡