መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 28

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ዐለቴ ሆይ፣ ችላ አትበለኝ፡፡ አንተ ዝም ካልኸኝ ወደ መቃብር ከሚወርዱ ጋር እሆናለሁ፡፡
2እንድትረዳኝ ወደ አንተ በጮኽኩ ጊዜ እጆቼን ወደ ቅዱስ ማደሪያህ በዘረጋሁ ጊዜ የልመኛዬን ቃል ስማ፡፡
3ከዐመፀኞች ጋር፣ ክፋትን ከሚያደርጉ ጋር፣ በልባቸው ክፉ ሐሳብ እያለ ከባልንጀራቸው ጋር በሰላም ከሚናገሩ ጋር ጐትተህ አትውሰደኝ፡፡
4የእጃቸውን ስጣቸው፣ እንደ ዐመፃቸውም ክፈላቸው እንደ ክፉ ተግባራቸው መልስቸው፡፡
5ለያህዌ ሥራ ግድ ስለሌላቸው፣ ለእጆቹም ተግባር ስፍራ ስላልሰጡ እርሱ ያፈርሳቸዋል፤ መልሶም አይሠራቸውም፡፡
6የልመናዬን ቃል ሰምቶአልና ያህዌ ይባረክ፡፡
7ያህዌ ብርታቴና ጋሻዬ ነው ልቤ በእርሱ ይተማመናል፤ እርሱም ረዳኝ፡፡ ስለዚህ ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ፡፡
8ያህዌ የሕዝቡ ብርታታቸው ነው ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው፡፡
9ሕዝብህን አድንን ርስትህንም ባርክ እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ተንከባከባቸው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።