መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 26

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ ያለ ነቀፋ ተመላልሻለሁና አንተው ፍረደኝ፤ ያለ ማወላውል በያህዌ ተማምኛለሁ፡፡
2ያህዌ ሆይ፣ ፈትነኝ መርምረኝም የልቤንና የውስጤን ንጽሕና ፈትን!
3የኪዳን ታማኝነትህ ዘወትር በፊቴ ነው በታማኝነትህም ተመላለስሁ፡፡
4ከአታላይ ሰዎች ጋር አልተባበርሁም ከማይታመኑ ሰዎችም ጋር አልተቀላቀልሁም፡፡
5የክፉዎችን ኅብረት ጠላሁ ከዐመፀኞችም ጋር አልተቀመጥሁም፡፡
6እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ ያህዌ ሆይ፣ መሠዊያህንም እዞራለሁ
7የምስጋናህን መዝሙር እየዘመርሁ ድንቅ ሥራዎችህን ሁሉ አወራለሁ፡፡
8ያህዌ ሆይ፣ የምትኖርበትን ቤት፣ የክብርን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ፡፡
9ነፍሴን ከኃጢአተኞች ጋር፣ ሕይወቴንም ደም ከተጠሙ ጋር አታጥፉ
10በእነርሱ እጅ የተንኰል ዕቅድ አለ ቀኝ እጃቸውም ጉቦ ያጋብሳል፡፡
11እኔ ግን በታማኝነት እጓዛለሁ አድነኝ፤ ምሕረትም አድርግልኝ፡፡
12እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል በጉባኤ ፊት ያህዌን እባርካለሁ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።