1ምድርና በእርሷ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የያህዌ ነው፡፡
2እርሱ ባሕር ላይ መሥርቶአታልና በውሆችም ላይ አጽንቶአታል፡፡
3ወደ ያህዌ ተራራ ማን ይወጣል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
4ንጹሕ እጅና ንጹሕ ልብ ያለው፣ ነፍሱን ለሐሰት ያላስገዛ በሐሰት የማይምል፣
5እርሱ ከያህዌ ዘንድ በረከትን፣ ከመድኃኒቱም አምላክ ጽድቅን ይቀበላል፡፡
6እርሱን የሚፈልግ ትውልድ የያዕቆብ አምላክን ፊት የሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው፡፡ ሴላ
7እናንተ ደጆች ራሳችሁን ቀና አድርጉ እናንተ የዘላለም በሮች የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
8ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ብርቱና ኃያል የሆነው ያህዌ፣ በጦርነት አሸናፊ የሆነው ያህዌ ነው፡፡
9እናንተ ደጆች ራሳችሁን ቀና አድርጉ እናንተ የዘላለም በሮች የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የሰራዊት ጌታ ያህዌ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው፡፡ ሴላ