1ያህዌ እረኛዬ ነው፤ ምንም አላጣም፡፡
2በለመለመ መስክ ያሳድረኛል ፀጥ ባለ ውሃ ዘንድ ይመራኛል፡፡
3ነፍሴን ይመልሳታል፤ ያድሳታል፡፡ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ ይመራኛል፡፡
4በጨለማው የሞት ሸለቆ ውስጥ እንኳ ባልፍ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፡፡
5በጠላቶቼ ፊት ለፊት በፊቴ ገበታ አዘጋጀህልኝ ራሴን በዘይት ቀባህ ጽዋዬ ሞልቶ ተርፏል፡፡
6በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ደግነትና ፍቅር ዘወትር ከእኔ ጋር ይሆናሉ፤ በያህዌም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ፡፡