መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 20

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በመከራ ቀን ያህዌ ይስማህ የያዕቆብም አምላክ ይጠብቅህ፡፡
2ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ
3መባህን ሁሉ ያስብልህ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ፡፡
4የልብህን መሻት ይስጥህ ዕቅድህንም ሁሉ ያሳካልህ፡፡
5በአንተ ደስ ይለናል በአምላካችንም ስም ዐርማችን ከፍ ከፍ እናደርጋለን፡፡ ያህዌ የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ፡፡
6ያህዌ የቀባውን እንደሚያድን አሁን ዐወቅሁ፤ ማዳን በሚችለው ቀኝ እጁ ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል፡፡
7አንዳንዶች በሰረገላ ሌሎች በፈረስ ይታመናሉ እኛ ግን የያህዌን ስም እንጠራለን፡፡
8እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ እኛ ግን ተነሣን፤ ቀጥ ብለንም ቆምን!
9ያህዌ ሆይ፣ ንጉሡን አድን ስንጠራህ እኛንም ሰማን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።