መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 17

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርበውን ጸሎት ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፡፡ ከሐሰተኛ ከንፈር ያልወጣውን ጸሎቴን አድምጥ፡፡
2ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤ ዐይኖችህም ፍትሕን ይመልከቱ፡፡
3ልቤን ብትመረምር፣ በሌሊትም ብትጐበኘኝ፣ ብትፈትነኝም ከእኔ ዘንድ ክፋት አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም፡፡
4የሰው ልጆችን ተግባር በተመለከተ አንተ በተናገርኸው ቃል መሠረት ከዐመፀኞች መንገድ ራሴን ጠብቄአለሁ፡፡
5አረማመዱ በመንገድህ ጸንቶአል እግሮቼም አልተንሸራተቱም፡፡
6ያህዌ ሆይ፣ ስለምትመልስልኝ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ጸሎቴንም ስማ፡፡
7የሚተማመኑብህን በቀኝህ ከጠላቶቻቸው የምታድናቸው አንተ ታማኝትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው፡፡
8እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሥር ሰውረኝ፡፡
9ከሚያስጨንቁኝ፣ ከከበቡኝም አደገኛ ጠላቶቼ ጋርደኝ፡፡
10እነርሱ ማንንም አይምሩም፤ አንደበታቸው ትዕቢትን ይናገራል፡፡
11ጠላቶቼ አስጨነቁኝ፤ ከበባም አደረጉብኝ መሬት ላይ ሊዘርሩኝም አፈጠጡብኝ፡፡
12እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚጓጓ፣ አድፍጦም እንደሚጠብቅ ደቦል አንበሳ ናቸው፡፡
13ያህዌ ሆይ፣ ተነሣና አጥቃቸው፤ በአፍጢማቸው ድፋቸው! በሰይፍህ ከክፉዎች አድነኝ፡፡
14ያህዌ ሆይ፣ እንዲህ ካሉ ሰዎች፣ ብልጽግናቸው በዚህ ሕይወት ብቻ ከሆነ ከዚህ ዓለም ሰዎች በቀኝህ አድነኝ፡፡ የአንተ የሆነ ሰዎችን ሆድ በመልካም ነገር ትሞላለህ እነርሱም ብዙ ልጆች ይኖሩዋቸዋል፤ ሀብታቸውንም ለልጆቻቸው ያወርሳሉ፡፡
15እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ ስነቃም ክብርህን ዐይቼ እረካለሁ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።