መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 16

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በአንተ ተማምኛለሁና ያህዌ ሆይ ጠብቀኝ፡፡
2ያህዌን፣ «አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ ውጪ መልካም ነገር የለኝም» አልሁት፡፡
3በምድር የሚኖሩ ቅዱሳን የተከበሩ ናቸው፤ በእነርሱም ደስ ይለኛል፡፡
4ሌሎች አማልክትን የሚከተሉ መከራቸው ይበዛል እኔ ግን ለአማልክቶቻቸው የደም ቁርባን አላፈስም፤ ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፡፡
5ያህዌ የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ ፍጻሜዬም በአንተ እጅ ነው፡፡
6መለኪያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል በእርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ፡፡
7የሚመክረኝን ያህዌን እባርካለሁ፤ ሌሊት እንኳ ልቦናዬ ያስተምረኛል፡፡
8ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስለሆነ አልናወጥም!
9ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፤ ክብሬም ሐሤት አደረገ፡፡ በእርግጥ ያለ ስጋት እኖራለሁ፡፡
10ምክንያቱም አንተ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም ታማኝህ መበስበስ እንዲደርስበት አታደርግም፡፡
11የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍስሐ አለ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።